የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የፖሊስ ሰራዊቱን በልዩ ልዩ ሙያዎች በማሰልጠን ለክልሉ ህዝብ ሰላም እና ደኅንነት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የፖሊስ ሰራዊቱን በልዩ ልዩ ሙያዎች በማሰልጠን ለክልሉ ህዝብ ሰላም እና ደኅንነት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለወንጀል ታክቲክ ምርመራ፣ ለመንገድ ላይ ትራፊክ ደህንነት፣ ለመረጃና ክትትል ባለሙያዎች እንዲሁም ለተመላሽ የፖሊስ ሰልጣኞች አቀባበል አድርጓል፡፡

ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት የእንኳን ደህና መጣቹህ መልዕክት አስተላልፈዋል።

እንደ ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ ገለጻ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ብቃት ያላቸው መምህራን እና አካል ብቃት አሰልጣኞች ያሉት በመሆኑ በርካታ የፖሊስ አመራር እና አባላትን እንዲሁም ባለሙያዎችን አሰልጥኖ ለክልሉ ህዝብ ሰላም እና ደኅንነት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

በመሆኑም እናንተ ወደ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ የመጣቹህ ሰልጣኞች ሙያው የሚፈልገውን ብቃት ይዛቹህ ትወጣላችሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ስልጠናውን በስኬት ለማጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁን ህግና ስርዓት ማክበር ይጠበቅባችኋል ሲሉ ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሰው ሃብት ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አብዮት ሽፈራው የክልላችን የፖሊስ ኃይል ለክልሉ ሰላምና ደህንነት እራሱን መስዋት እያደረገና የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ ቀን ከሌት እየተጋ ይገኛል ብለዋል፡፡

በስልጠናው የምታገኙትን ሙያዊ ብቃት ተጠቅማቹህ ማህበረሰቡን በቅንነት እና በታማኝነት እንድታገለግሉ በማለት አሳስበዋል፡፡

ሰልጣኞች በበኩላቸው የሚሰጠንን የሙያ ስልጠና በአግባቡ ተጠቅመን ሳይንሳዊ የሆነ አሰራርን በመከተል ለማህበረሰቡን በፍትሐዊነት አገልግሎት እንሰጣለን ብለዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top