ዋና ሳጅን የኔነሽ ሽመክት ጣሊያን ሀገር በተካሄደ ሀገር አቋራጭ ውድድር አሸነፈች።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የአትሌቲክስ ቡድን አባል የሆነችው ዋና ሳጅን የኔነሽ ሽመክት ጣሊያን ሀገር በተካሄደ ሀገር አቋራጭ ውድድር አንደኛ በመውጣት አሸናፊ ሆናለች።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የአትሌቲክስ ቡድን አባላት በተለያዩ ውድድሮች ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የሀገራችን፣ የክልላችን እና የተቋማችን ስም በአለም አደባባይ በማስጠራት አርበኛ እየሆኑ ይገኛሉ።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እና የዋና ጠቅላይ መምሪያው የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ ለመላው የክልሉ ፖሊስ ሰራዊት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክ አስተላልፏል።


