የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አትሌቲክስ ቡድን አባል የሆነው ኮንስታብል ይስማው ድሉ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸናፊ ሆነ።
በ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አትሌቲክስ ቡድን አባል የሆነው ኮንስታብል ይስማው ድሉ 1ኛ በመውጣት የ400 ሺህ ብር እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
ሌላኛው የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አትሌቲክስ ቡድን አባል የሆነው ዋና ሳጅን ድንቅዓለም አየለ ደግሞ 3ኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቁ የ100 ሺህ ብር እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
ኮንስታብል ይስማው ድሉ በባለፈው ዓመት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 3ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል።
በ2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ ውድድር ላይ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አትሌቲክስ ቡድን አባል የሆኑት ኮንስታብል ይስማው ድሉ እና ዋና ሳጅን ድንቅዓለም አየለ ባስመዘገቡት ድል የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለመላው የክልሉ ፖሊስ ሰራዊት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።



