ለህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኑ ሊደርስ የነበረ ዲሽቃ እና ስናይፐር በቁጥጥር ስር ዋለ።

ለህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኑ ሊደርስ የነበረ ዲሽቃ እና ስናይፐር በቁጥጥር ስር ዋለ።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ላይ አርማጭሆ ወረዳ በተደረገ የኬላ ፍተሻ ታጣቂ ቡድኑ ሊደርስ የነበረ ዲሽቃ እና ስናይፐር በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ደሳለኝ አበራ ተናግረዋል።

መነሻውን አብርሃ ጅራ አድርጎ ወደ ባህርዳር እየተጓዘ በነበረ ሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 1 አማ 43698 በሆነ ባጃጅ ሲያጓጉዙ የነበሩ 2 ተጠርጣሪዎች 1 ዲሽቃ እና 1 ስናይፐር በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ላይ አርማጭሆ ወረዳ በተለምዶ አርገበራ እየተባለ በሚጠራው የኬላ ፍተሻ ጣቢያ ላይ በወረዳው ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ኮማንደር ደሳለኝ አበራ አሳውቀዋል።

ፖሊስ ዲሽቃው እና ስናይፐሩ በጠላት ዕጅ እንዳይገባ በማድረጉ በህዝብ ላይ ሊደርስ የሚችልን ከፍተኛ ጉዳት ማስቀረት ተችሏል ነው ያሉት የፖሊስ መምሪያ አዛዡ።

ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ አፋጣኝ መዝገብ አደራጅቶ ምርመራ ማጣራት መጀመሩን ኮማንደር ደሳለኝ አበራ አሳውቀዋል ።

ህብረተሰቡ የህገ-ወጦችን እንቅስቃሴ በንቃት በመከታተልና ለጸጥታ መዋቅሩ መረጃ በመስጠት የተለመደ አጋርነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ሲሉ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ደሳለኝ አበራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top