በባህርዳር ዙርያና ሰሜን ጎጃም ዞን በተደረገ ኦፕሬሽ በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል መቀናጀቱን የአማራ ክልል የጋራ ጸጥታ ግብር-ኃይል አስታወቀ።

በባህርዳር ዙርያና ሰሜን ጎጃም ዞን በተደረገ ኦፕሬሽ በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል መቀናጀቱን የአማራ ክልል የጋራ ጸጥታ ግብር-ኃይል አስታወቀ።

እንደ ግብር-ኃይል መግለጫ፣ የምስራቅ ዕዝ እና የክልሉ የጸጥታ ኃይል የጋራ እቅድና ስምሪት በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል የተገኝበት እና በርካታ የጠላት ኃይል ከጥቅም ውጭ የተደረገበት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ከምስራቅ ዕዝ አሀዶች ኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ እንዲሁም የአማራ ክልል አድማ መከላከል እና መደበኛ ፖሊስ፣ የክልሉ ሚሊሻና ሰላም አስከባሪ በጋራ ባደረጉት ኦፕሬሽን ከ90 በላየይ ህገ-ወጥ የታጣቂ ቡድኖች ከጥቅም ውጪ ተደርገዋል፡፡

ህገ-ወጥ የታጣቂ ቡድኖች በባህርዳር ዙሪያ ባሉ ገጠራማ አካባቢዎችና የሰሜን ጎጃም ዞን የገጠር ወረዳዎች አካባቢ በማገትና ገንዘብ በመቀበል፣ የመኪና አስቁሞ ዘረፋ በማድረግ፣ ቀረጥ በማስከፈል፣ ህዝቡ ከወንጀል ስጋት ነጻ ሆኖ መንቀሳቀስና ተግባሩን መፈፀም እንዳይችል ሲያደርጉ መቆየታቸው ተጠቅሷል።

በመሆኑም ምስራቅ ዕዝ ከፍተኛ አመረሮችና ከአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዦች በጋር በኦፕሬሽን እቅዱ ላይ ውይይት ተካሂዶና ግልፀኝነት በመፍጠር በግዳጁ ሌሎች ዩኒቶችና ከአየር ወለድ ክፍለጦር ንስር ሻለቃ ጋር በጥምረት አካባቢውን የማጽዳት ግዳጅ ተወጥተዋል፡፡

ይህ ከጥቅምት 27 ቀን 2018 እስከ ህዳር 02 ቀን 2018 ዓ.ም ለስድስት ተከታታይ ቀናት የፀረ-ሽምቅ ስምሪት የተደረገው በባህርዳር እና አካባቢው፣ በሰሜን ጎጃም እና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች በሚገኙ የተለያዩ ወረዳ እና ቀበሌዎች መሆኑ ተገልጿል።

ስምሪቱን እንዲያስተባብሩ ከተመደቡት አመራሮች ውስጥ ብርጋዲየር ጄኔራል አዲሱ መሐመድ፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር አበበ ውቤ እና የአየር ወለድ ክፍለጦር፣ ንስር ሻለቃ አዛዥ ሻለቃ አስናቀ መርዕድ በሰጡት ማብራሪያ በጥምረት በተደረገው ኦፕሬሽን 27 ህገ-ወጥ ታጣቂዎች ላይ ርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን፣ ስምንት ቆስሏል፣ 61 ተማርኳል እንዲሁም አመራሮችን ጨምሮ ስምንት እጅ ሰጥተዋል፡፡

ህገ-ወጥ ቡድኑ ሲጠቀምበት የነበረ 58 ኤ ኬ ኤም ክላሽ፣ 90 የቃታ መሳሪያ፣ 11 ሽጉጥ፣ 05 ቦምብ፣ 1 ሺ 281 ልዩ ልዩ የጥይት ዓይነቶች እንዲሁም ስድስት በሞባይል ሲስተም የሚፈነዳ ፈንጂ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በአጠቃላይ ይህ አፕሬሽን ጠላት ከፍተኛ በሆነ የስነ-ልቦና ጫና ውስጥ ገብቶ እንዲኮላሽ እና ተረጋግቶ እንዳይንቀሳቀስ ያደረገ ሲሆን ጥምር ጦሩ እግር-በእግር እየተከተለ እየማረከ ጠላት ይዞት የነበረውን አካባቢ የማጽዳት ስራ መሰራቱን የጥምር ጦሩ አመራሮች ተናግረዋል።

እንደ አዛዦቹ ገለጻ ይህ ውጤት የተገኘው አስቀድሞ ሁሉም የጸጥታ አመራሩ በእቅዱ ላይ በመወያየትና ቀጣናዎችን በጋራ ለይቶ ክፍፍል በማድረግ ወደ ስራ በመገባቱ የአመራሩም ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ ተናቦና ተግባብቶ በቅንጅት ግዳጁን በመፈጸሙ የተገኝ ውጤት መሆኑ አክለው አብራርተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top