በወረኢሉ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እጃቸውን ሰጥተዋል።
በተሳሳተ መንገድ ጫካ ገብተው የነበሩ ራሱን ዋስል ክፍለ ጦር ሰንጥቅ ሻለቃ ብሎ የሚጠራው የሻለቃ አዛሽ ቃሉ አስፋው እና የሻለቃ ዘመቻ ኃላፊ ሱልጣን ሲሳይን ጨምሮ ሌሎች ህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኖች ለጥምር ጦሩ እጃቸውን ሰጥተዋል።
ታጣቂዎቹ የጫካ ትግል የህዝቡን ችግር የማይፈታ መሆኑን በመገንዘብ የበደሉትን ማህበረሰብ ለመካስ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
ጥምር ጦሩ ላደረገላቸው አቀባበል ምስጋና ያቀረቡት ህገ-በጥ ታጣቂዎች በጫካ የሚገኙ ጓደኞቻቸውም የሰላምን አማራጭ እንዲከተሉና እድሉን እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።
በሰላም እጃቸውን የሰጡ ታጣቂዎች ስናይፐር፣ የጦር ሜዳ መነጽር፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች እና የወገብ ትጥቆችን ለመንግስት አስረክበዋል።



