በገንዳውኃ ከተማ አስተዳደር 3ሺህ 124 ህገ-ወጥ የክላሽ ጥይት በፍተሻ መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።

በገንዳውኃ ከተማ አስተዳደር 3ሺህ 124 ህገ-ወጥ የክላሽ ጥይት በፍተሻ መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።

በምዕራብ ጎንደር ዞን በገንዳውኃ ከተማ አስተዳደር በቀበሌ 01 ከአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ 3ሺህ 124 የክላሽ ጥይት መያዙን ፖሊስ ገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ሀይሌ ብርሃኑ ተተኳሽ ጥይቱ የተያዘው ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ጥናት ነው ብለዋል።

እንደ ምክትል ኢንስፔክተር ሀይሌ ገለጻ ከፍርድ ቤት የመፈተሻ ፍቃድ በመያዝ የገንዳውኃ ከተማ ነዋሪ ከሆኑት ከአቶ ተንሳይ ሽጉጥ መኖሪያ ቤት ነው 3ሺህ 124 ህገ-ወጥ የክላሽ ጥይት መያዙን ያብራሩት።

ፖሊስ ወንጀልን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የማህበረሰቡ እያደረገ ላለው ተሳትፎ እና ቀና ትብብር የፖሊስ አዛዡ ምስጋና አቅርበዋል።

ህገ-ወጥ ድርጊቶች ለህዝብ ደኅንነት ስጋት በመሆናቸው ህብረተሰቡ ለፖሊስ ሰራዊቱ የተለመደ ትብብሩን በማድረግ እና ጥቆማ በመስጠት ለወንጀል መከላከል ስራ ውጤታማነት የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ ሲሉ ምክትል ኢንስፔክተር ሀይሌ ብርሃኑ የገንዳውኃ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top