ለአማራ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ አመራርና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው የወንጀል መረጃና ክትትል ስልጠና ተጠናቀቀ

ለአማራ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ አመራርና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው የወንጀል መረጃና ክትትል ስልጠና ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከአማራ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመተባበር ለክልሉ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው የወንጀል መረጃና ክትትል ስልጠና ተጠናቋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) በፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የህዝቡንና የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ስልጠናውን እንደመነሻነት በመውሰድ እና ያገኛችሁትን እውቀትና ልምድ ተጠቅማችሁ በማስፋት በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማምጣት በትኩረት መስራት ይጠበቅባችኋል ሲሉ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ለሰልጣኞች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ታምራት ሙሉጌታ በበኩላቸው በስልጠና ቆይታችሁ ያገኛችሁትን ዕውቀትና ክህሎት ተጠቅማችሁ ለሀገርና ለህዝብ ፍላጎት ቅድሚያ በመስጠት የተጣለባችሁን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ይገባችኋል ብለዋል፡፡

ሰልጣኞቹ ክልሉ በሚፈልገውና ባቀረበው የስልጠና አይነት መሰረት ከሙያው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው የስልጠና ፓኬጅ ተዘጋጅቶ እንደተሰጣቸው እና በስልጠና ቆይታቸውም መልካም ዲሲፕሊን የነበራቸው እንደነበር በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአመራርና አቅም ግንባታ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸው ተናግረዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top