የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ቀጣይ በሚሰጣቸው ልዩ ልዩ ስልጠናዎች ላይ የዕቅድ ውይይት አካሂዷል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ቀጣይ በሚሰጣቸው ልዩ ልዩ ስልጠናዎች ላይ የዕቅድ ውይይት አካሂዷል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከምንጊዜውም በላይ በእውቀት፣ በክህሎት እና በፖሊሳዊ ብቃቱ የተመሰከረለት የፖሊስ ኃይል ለማፍራት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ አዲስ ለሚቀበላቸው የታክቲክ ወንጀል ምርመራ፣ የመንገድ ላይ ትራፊክ ደህንነትና የወንጀል መረጃና ክትትል ባለሞያዎች የስልጠና ማስፈጸሚያ እቅድ ላይ በስፋት ተወያይቷል።

የውይይቱን መነሻ ሀሳብ ያቀረቡት የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ የልዩ የልዩ የፖሊስ ሙያዎች ስልጠና መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ዳንኤል ንጉሴ በውይይቱ በርካታ ሀሳቦችን አንስተዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ በየጊዜው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም በርካታ ስልጠናወችን ሲሰጥ መቆየቱን አንስተዋል።

በቀጣይም ለምንሰጣቸው ስልጠናወች ሁሉም የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ሰራተኞች የሚጠበቅባቸውን ሙያዊ ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡም ምክትል ኮሚሽነር አበበ አሳስበዋል።

የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ሰራተኞች በበኩላቸው የተሰጠንን ተልዕኮ በመወጣት ተቋሙን ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ጠንክረን እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top