ታጥቀው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የታጣቂ የቡድኑ አባላት የሠላም አማራጭን ተቀብለው ገቡ።
በደቡብ ጎንደር ዞን በፎገራ ወረዳ በአለምበር እና ወጅ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የታጣቂ ቡድኑ አባላት የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የገቡ ሲሆን የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የጸጥታ ተቋማት ኃላፊዎችና የአድማ መከላከል አመራሮች ተገኝተዋል።
ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጎን ተሰልፈን ህዝባችን አንወጋም ያሉት በአርበኛ ጌታሁን ሙጬ (ጫካ) ይመሩ የነበሩ 12 የቡድኑ አባላት የሰላም አማራጭን ተቀብለው እጃቸውን ሰጥተዋል።
የውጭ ባዕዳና የውስጥ ባንዳዎች ተላላኪ ልንሆን አንችልም። ስለሆነም በቀጣይ ህዝባችን ለበደልነው ጥፋት ለመካስም ዝግጁ ነን ብለዋል።
ሁለት ብሬን፣ አንድ የቃታ መሳሪያ እና 7 ክላሽ በመያዝ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የገቡት የታጣቂ ቡድኑ አባላት የጦር መሳሪያቸውን ለደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ አመራሮችና ለአድማ መከላከል አመራሮች አስረክበዋል።







