በ31ኛው የመላው አማራ ሀገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር የአማራ ክልል ፖሊስ አትሌቲክስ ቡድን በአጠቃላይ ውጤት አሸናፊ በመሆን አጠናቋል።
31ኛው የመላው አማራ ሀገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር በደብረ ማርቆስ ከተማ ተካሂዷል።
በዚህ ውድድር ተሳታፊ የሆነው የአማራ ክልል ፖሊስ አትሌቲክስ ቡድን በዱላ ቅብብል፣ በድብልቅ ሪሌ ወንድና ሴት እንዲሁም በ10 ኪ.ሜ ሴቶች እና በ8 ኪ.ሜ ወንዶች ተሳትፈን ሶስት ዋንጫ፣ 2 ነወርቅ፣ 2 የብር፣ 2 የነሀስ ሜዳሊያዎችን አግኝቷል።
የአማራ ክልል ፖሊስ አትሌቲክስ ቡድን በውድድሩ የበላይቱን በመያዝ በአጠቃላይ ውጤት 1ኛ ሆኖ አጠናቋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለመላው የክልሉ ፖሊስ ሰራዊት እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል።



