የአማራ ክልል ፖሊስ ሰላምና ልማት ማህበር የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት አፈፃፀምና በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ሰላምና ልማት ማህበር የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት አፈፃፀምና በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

ማህበሩ ባለፈው በጀት ዓመት ያከወናቸውን ተግባራት አስመልክቶ ሪፖርት ያቀረቡት የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሰው ኃብት አስተዳደርና ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊና የማህበሩ ቦርድ ሰብሳቢ ረዳት ኮሚሽነር አብዮት ሽፈራው ማህበሩ በበጀት ዓመቱ ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገቡን አንስተዋል።

ማህበሩ በሞት፣ በጡረታና በቦርድ ለሚሰናበቱ አባላት በርካታ ክፍያዎችን የፈጸመ ሲሆን በገቢ ማሰባሰቢያ ዙሪያም የተሻለ አፈፃፀም ማሳየቱን ረዳት ኮሚሽነር አብዮት ሽፈራው አክለው ተናግረዋል።

በቀጣይ የአባላትን ቁጥር በመጨመር እና ወጭን በመቀነስ የገቢ ማሰባሰብ ስርዓትን በማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ማህበሩ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ዕቅድ አዘጋጅቶ ስራ የጀመረ ሲሆን ከክልል እስከ ወረዳ ያለውን የገቢ አሰባሰብ ሂደት ቀልጣፋ እና ዘመናዊ በማድረግ አቅምን ማሳደግ ቀዳሚ ተግባር ነው ብለዋል።

የማህበሩ የ2017 ዓ/ም የገቢ መጠን ከባለፈው 2016 ዓ/ም በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ውጤት መመዝገቡም በሪፖርቱ ተመላክቷል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top