“ጽናት፣ ጀግንነት እና ለአላማ መስዋዕትነት የተቋማችን መገለጫ ነው።”
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ የፖሊስ ሰራዊት አመራርና አባላት የእውቅና እና የሽልማት መርሐ-ግብር እያካሄደ ነው።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሪፎርም አካል የሆነውና በግዳጅ እና በልዩ ልዩ ተልዕኮዎች ተሰማርተው በህግ ማስከበር ታላቅ ጀብድ የፈፀሙ ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ የሚገኙ አመራርና አባላትን እንዲሁም የላቀ ስራ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ስትራቴጂክ አመራሮች የእውቅና እና ሽልማት መርሐ-ግብር በመካሄድ ላይ ነው።
በመርሐ-ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፋ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋየ፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በዚህ መርሐ-ግብር ወንድ=3096 ሴት=107 በድምሩ= 3203 የሰራዊቱ አመራር እና አባላት ዕውቅናና ሽልማት የሚያገኙ ይሆናል።















