ከመደበኛ የበጀት አስተዳደር ስርዓት ወደ ፕሮግራም ዝግጅት በጀት አስተዳደር ስርዓት ለመሸጋገር የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ።

ከመደበኛ የበጀት አስተዳደር ስርዓት ወደ ፕሮግራም ዝግጅት በጀት አስተዳደር ስርዓት ለመሸጋገር የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ።

ለአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለዕቅድና በጀት መምሪያ እንዲሁም ለግዥና ፋይናንስ መምሪያ አመራሮች እና ባለሙያዎች ነው ለሁለት ቀናት የቆየ ስልጠና የተሰጠው።

ከፌዴራል ፖሊስ እና ከገንዘብ ሚኒስቴር የመጡ የዘርፉ አመራሮች እና ባለሙያዎች ናቸው ስልጠናውን የሰጡት።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ በዕለቱ ተገኝተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ስልጠናው የተሻለ የበጀት አስተዳደር ስርዓትን ለማጎልበት አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

ከስልጠናው ጥሩ ግንዛቤ በመውሰድ ተቋሙ ያሉበትን የበጀት አያያዝ ሁኔታ ለማሻሻል ያስችላል ነው ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ።

ኮማንደር ሰላሞን ታደሰ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዕቅድና በጀት መምሪያ የበጀት ዋና ክፍል ኃላፊ እንደተናገሩት በክልሉ የመጀመሪያ ነው የተባለለት ይህ የፕሮግራም ዝግጅት በጀት ከመደበኛ በጀት አንፃር ስራን ከበጀት ጋር በማዛመድና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

የጸጥታ ስራዎችን ለመከወን የሚመደብን በጀት በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉንን ለመከታተል አመች ነው የሚሉት ኮማንደር ሰለሞን የበጀት አያያዝና አጠቃቀም ስርዓትንም ያዘምናል ሲሉ ነው አክለው ያብራሩት።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top