የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የእግር ኳስ ስፖርት ቡድን አባላት የተቋሙን የሪፎርም ስራ ጎበኙ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የእግር ኳስ ስፖርት ቡድን አባላት የተቋሙን የሪፎርም ስራ ጎበኙ።

ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ በጉብኝቱ ወቅት ተገኝተው እንደተናገሩት ተቋሙ ያከናወነው ሁለንተናዊ የሪፎርም ስራ በሁሉም የስራ ክፍሎች ተጨባጭ ውጤቶችን ሊያመጣ የሚያስችል ነው ብለዋል።

በስፖርት ዘርፉ የተሰሩ ስራዎች በቀጣይ ጥሩ ውጤቶችን እንደሚያመጡ ተስፋ የተጣለባቸው ናቸው ሲሉ ምክትል ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

የስፖርት ቡድኑ በርካታ ድሎችን በማስመዝገብ ታሪክ የሰራ ነው ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ ከዚህ የበለጠ ውጤት እንዲያመጣም በተቋሙ በኩል አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።

የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ በበኩላቸው የተቋሙ ስፖርት ቡድን አስራ አራት ዓመታትን በስኬት ተጉዞ በርካታ ድሎችን ያስመዘገበ ቡድን ነው ብለዋል።

አሁን ላይ የስፖርት ቡድኑ ተቋሙ ያደረገውን የሪፎርም ስራና ያለበትን የከፍታ ዘመን ጉዞ ማየቱ ለበለጠ ውጤት ማስመዝገብ ግብዓት ይሆነዋል ሲሉ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ አክለው ተናግረዋል።

የስፖርት ቡድኑ ተጨዋቾችና አሰልጣኞችም የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ያከናወነው የሪፎርም እና የተቋም ግንባታ ስራ እጂግ እንዳስደሰታቸው እና ተቋሙ ወደ ከፍታ ዘመን እያደረገው ያለው ጉዞ ከሌሎች ተቋማት ጋር ያለውን ተወዳዳሪነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

የስፖርት ቡድኑ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሞራል ተነሳሽነትን እንደፈጠረላቸው እና ጠንክረው ለመስራትም ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ስፖርት ቡድኑ አባላት ከክረምቱ የእረፍት መልስ ነው የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ያደረገውን ሁሉን አቀፍ የሪፎርም ስራና አዲሱን ህንፃ የጎበኙት።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top