ሰላምን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ገለጸ
የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ከፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አባላት እና አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ላይ ኮማንደር ተሾመ ብዙ የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ውይይቱ በህግ ማስከበር፣ ሰላምን በማስጠበቅ፣ ኅብረተሰቡን ያሳተፈ የወንጀል መከላከል ስራዎችን፣ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ቁጥጥር እንዲሁም የግዳጅ አፈጻጸም ተግባራት ላይ ያተኮረ ነው።
በ2017 ዓ.ም የነበሩ ጠንካራ እና ደካማ አፈፃፀሞችን በመለየት በቀጣይ የማህበረሰቡን ዘላቂ ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አባላት እና አመራሮች ገልጸዋል።
የማህበረሰቡን ተሳትፎ በማጎልበት እና የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል አደረጃጀትን በማጠናከር የከተማውን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ እንደሚሰሩ አብራርተዋል።
የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አባላት እና አመራር ሰላምን ለማስፈን እያከናወኑ ላለው ተግባር የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ምስጋናውን አቅርቧል።







