በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ጃራ ድልድይ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የትራፊክ አደጋ መድረሱን ፖሊስ ገልጿል።

ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ተሽከርካሪ ባስ ከጭነት መኪና ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የደረሰው ሲል ነው የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ያስታወቀው።

በደረሰው አደጋም እስከ አሁን የ8 ሴት እና የ3 ወንድ በድምሩ የ11 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ያለፈ ሲሆን በ23 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ነው ፖሊስ ጨምሮ ያስታወቀው።

በአሁኑ ሰዓት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በጨፋ ሮቢት ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ እያጣራ እንደሆነም ፖሊስ ገልጿል።

አሽከርካሪዎች ህግና ስርዓትን አክብረው በማሽከርከር በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ መከላከል እንደሚገባም ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top