በመላው አማራ ክልል በተወሰደ ህግን የማስከበር ተግባር ድል ተመዝግቧል።
ከመስከረም 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ጀግናው የአድማ መከላከል ፖሊስ እንዲሁም ሌሎች የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ጋር በጋራ በወሰዱት ህግ የማስከበር ዘመቻ ድልን ተቀናጅተዋል።
በዚህም በሰሜን ወሎ ዞን፦ ጋሸና፣ መርሳ ከተማ ዋድላና ሀብሩ ወረዳ እንዲሁም በደቡብ ወሎ ዞን፦ ወረኢሉ፣ ከላላ፣ ወረባቦ፣ ቦረና፣ ተንታ፣ ኩታበር ወረዳዎች እና በመካነ ሰላም ከተማ፣ በጎጃም ቀጠና፦ በአዊ ባንጃ ወረዳ፣ በደምበጫ፣ በገርጨጭ እና በእንጅባራ የገጠር ቀበሌዎች እንዲሁም በማዕከላዊ፣ በሰሜን እና በደቡብ ጎንደር ዞኖች በተጨማሪም በሰሜን ሸዋ ዞን ታጥቀው የህዝብን ሰላምና ደኅንነት በሚነሱና በሚዘርፉ ህገ-ወጥ ቡድኖች ላይ ህጋዊ እርምጃ ከተወሰደባቸው አካባቢዎች ተጠቃሾች ናቸው።
በዚህም በበርካታ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን በርካቶችም ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነዋል።
በተጨማሪም በርካታ የጦር መሳሪያዎች፣ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ህገ-ወጥ ቡድኖች የሚጠቀሙባቸው ቁሳቁሶች ተማርከዋል።
የአማራን ህዝብ ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ ጥምር ጦሩ የሚያካሂደውን ህግ የማስከበር ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።






