ማህበረሰቡን ሲዘርፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

ማህበረሰቡን ሲዘርፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

በአዊ ብሔረሰብ ዞን በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር በማህበረሰቡ ላይ የማጭበርበር ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር የ1ኛ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር የኔው ፈቃዱ አስታውቀዋል።

ተጠርጣሪዎቹ የስርቆት እና የማጭበርበር ወንጀሎችን የሚፈጽሙት አደንዣዥ ዕጾችን ተጠቅመው በማፍዘዝ መሆኑንም አዛዡ አክለው ተናግረዋል።

ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ በርካታ የኤ.ቲ. ኤም ካርዶች እና ሎተሪ ደርሷችኋል በማለት የሚያጭበረብሩበት ህጋዊ ያልሆኑ ሎተሪዎችን ይዘው መገኘታቸውንም ምክትል ኢንስፔክተር የኔው ገልጸዋል።

ማህበረሰቡ አላስፈላጊ ጥቅም ለማግኘት ከሚደረግ ህገ-ወጥ ተግባር እራሳችሁን በማራቅ እና አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲመለከቱ በአቅራቢያቸው ለሚገኙ የህግ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ የፖሊስ አዛዡ ማሳሰባቸውን የአዊ ብሔረሰብ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል አስታውቋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top