ለመስቀል ደመራ በዓል ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ይፋ አድርጓል።

ለመስቀል ደመራ በዓል ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ይፋ አድርጓል።

በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ በባህርዳር ከተማ ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ይፋ አድርጓል፡፡

በመሆኑም የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ከዚህ በታች የተገለፁት መንገዶች ዝግ መሆናቸውን ተገንዝበው ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

በዚሁ መሠረት ከቀኑ 7፡ 00 ሰዓት ጀምሮ እስከ በዓሉ ፍፃሜ ድረስ፡-

• ከሳፍሪ ሞል እስከ አመዶ ገበያ

• ከድሮው ጊዮን ሆቴል ወይም ትራፊክ መብራት እስከ አዝዋ ሆቴል

• ከፋሲሎ ትምሕርት ቤት እስከ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት

• ከዲላኖ ሆቴል እስከ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ውስጥ ለውስጥ ያሉ መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ይሆናሉ።

ህብረተሰቡም ከፖሊስ የሚሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ጥሪውን አስተላልፏል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top