የጎንደር ቀጣና የሠላም እና የጸጥታ ጉዳዮች የውይይት መድረክ በጎንደር ከተማ ተካሄደ።

የጎንደር ቀጣና የሠላም እና የጸጥታ ጉዳዮች የውይይት መድረክ በጎንደር ከተማ ተካሄደ።

በጎንደር ከተማ በቀጣናው የወቅታዊ የሠላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

የውይይት መድረኩ ወቅታዊ የሰላም እና የጸጥታ ተግባራት አሁናዊ ሁኔታን የሚገመገምበት መሆኑ ተመላክቷል።

በጎንደር ቀጣና ያለው የሠላም እና ጸጥታ ሁኔታ በርካታ ለውጦች የታዩበት እንደሆነ በውይይት መድረኩ ተነስቷል። አሁን ያለውን ሠላም ዘላቂ እና አስተማማኝ ለማድረግ የሚያስችል የቀጣይ ጊዜያት ቁልፍ ሥራዎች ቀርበው በውይይት ተሳታፊዎች መግባባት ላይ ተደርሷል።

በቀጣይ ጊዜያት የቀጣናውንና የክልሉን ሰላም አስተማማኝ በማድረግ ማኅበረሰቡ በሠላም ወጥቶ እንዲገባ እና በሙሉ አቅሙ ወደ ልማት ሥራዎች እንዲዞር ሰላሙን አስተማማኝ ማድረግ እንደሚገባም በመድረኩ ተገልጿል።

በግምገማና በውይይት መድረኩ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎችና የጦር መሪዎች በመድረኩ መሳተፋቸውን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አስነብቧል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top