“ኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ የክልሉ ፖሊስ ሰራዊት ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል እየከፈለ ያለውን ሁለንተናዊ መስዕዋትነት እና የተቋሙን የሪፎርም ስራ ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ በኩል እንደ ድልድይ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።” ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ

“ኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ የክልሉ ፖሊስ ሰራዊት ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል እየከፈለ ያለውን ሁለንተናዊ መስዕዋትነት እና የተቋሙን የሪፎርም ስራ ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ በኩል እንደ ድልድይ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።” ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በዕለቱ የተገኙት የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ ኮሙዩኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ የክልሉን ፖሊስ ከማህበረሰቡ ጋር በማገናኘት ሰራዊታችን እያከናወነ ያለውን ሁሉን አቀፍ አገልግሎት ተደራሽ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ወንጀልን በመከላከል ረገድ ትልቅ ሚና የምትወጡ፣ ተቋሙን ከህዝብ ጋር የምታገናኙ የተቋሙ አይንና ጆሮ በመሆናችሁ ድርብ ኃላፊነትን የተሸከማችሁ በመሆናችሁ ለክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ዕቅድ መሳካት ሚናችሁ የጎላ ነው ብለዋል ምክትል ኮሚሽነሩ።

ዕቅዱ ያቀረቡት የኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር መሳይ ወርቁ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ዕቅድን መሰረት በማድረግ እንደ ኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ በሁሉም ዘርፎች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና፣ በቂ ሙያተኛን የማሟላት እንዲሁም በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው አሰራርን መተግበር ዋነኛ ዕቅዳችን ነው ብለዋል።

ሙያተኞችን በመመደብና አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት የህዝብ ግንኙነት ስራን ማጎልበት በትኩረት ከሚተገበሩ የቀጣይ ዓመት ዕቅዶች መካከል እንደሆነም ነው ኮማንደር መሳይ የገለፁት።

ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ ኃላፊ በበኩላቸው ዕቅዱ ግብ እንዲመታና ውጤታማ እንዲሆን ከባለሙያ እስከ አመራር ድረስ በትጋት እና በኃላፊነት ስሜት ስራዎችን መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

ዕቅዱ ሪፎርሙን ከምናሳልጥበት አሰራር አንዱ በመሆኑ መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች በማስተካከል ለተሻለ ነገ ዛሬ ላይ መስራትን የሚጠይቅ ነው ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም የተቀመጠው ዕቅድ ለመስራት ተስፋን የሰነቀ፣ ውጤት ሊያስገኝ የሚችልና አካታች መሆኑን ጠቅሰው ለዕቅዱ መሳካት በሁሉም ዘርፎች ተፈላጊውን ኃላፊነት በመወጣት የነበረንን የህዝብና የፖሊስ ተቋምን ድልድይ ሆኖ የማገናኘት ስራችንን የበለጠ ውጤታማ ማድረግ ይጠበቅብናል በማለት አብራርተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top