በሰላም እና በጸጥታ ጉዳዮች ላይ የሚመክር መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ ተካሄደ።

በሰላም እና በጸጥታ ጉዳዮች ላይ የሚመክር መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ ተካሄደ።

በወቅታዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች ላይ የሚመክር መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ ተካሂዷል።

መድረኩ አሁናዊ የሰላም እና የጸጥታ ሁኔታን የሚገመገምበት እንደሆነ ተገልጿል።

በወሎ ቀጣና ያለው የሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ በርካታ ለውጦች የታዩበት እንደሆነ በዕለቱ ተነስቷል።

ሰላሙን ዘላቂ እና አስተማማኝ ለማድረግ በቀጣይ የሚከናወኑ ቁልፍ ስራዎች ላይ መግባባት መደረሱም ተመላክቷል።

በቀጣይ ጊዜያት የክልሉን ሰላም አስተማማኝ በማድረግ ማኅበረሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ እና በሙሉ አቅሙ ወደ ልማት ስራዎች እንዲዞር ሰላሙን አስተማማኝ ማድረግ እንደሚገባም ተጠቁሟል።

በውይይት መድረኩ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር)፣ የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር)፣ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አሰፋ ቸኮልን ጨምሮ ሌሎች የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኀላፊዎች፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጄኔራል መኮንኖች፣ የዞን አስተዳዳሪዎች እና ከንቲባዎች እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የስራ መሪዎች ተሳትፈዋል።

በተመሳሳይ በትናንትናው እለት በደብረብርሃን ከተማ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የሸዋ ቀጠናን በአሁናዊ የሰላም እና የጸጥታ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top