ሪፎርሙን ውጤታማ በማድረግ የተጣለብንን ህዝባዊ ኃላፊነት ልንወጣ ይገባል ሲሉ የወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ ዞን ፖሊስ አመራሮች ተናገሩ።

ሪፎርሙን ውጤታማ በማድረግ የተጣለብንን ህዝባዊ ኃላፊነት ልንወጣ ይገባል ሲሉ የወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ ዞን ፖሊስ አመራሮች ተናገሩ።

በአማራ ክልል የወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ ዞን ፖሊስ መምሪያ የአመራር ምደባ አካሂዷል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ

እያካሄደ ያለውን ሪፎርም ተከትሎ የወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ ዞን ፖሊስ መምሪያ የዞን ዋና ክፍል ኃላፊ፣ የወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ እና የክፍል ኃላፊዎች ተመድበዋል።

ፖሊስ ህዝባዊ አደራ ያለበት ችግሮችን የሚፈታ እና የህዝብን ደኅንነት የሚያረጋግጥ ተቋም ነው ሲሉ ምክትል ኮማንደር ወለላው ተገኘ የወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ያካሄደው ሪፎርም ከግብ እንዲደርስ እና ተቋሙ ወደ ከፍታ እያደረገ ያለውን ጉዞ ለማስቀጠል በየደረጃው በሚገኝ አመራር እና አባላት በቁርጠኝነት ህዝብን ማገልገል ይጠበቅበታል ሲሉ አዛዡ አሳስበዋል።

ሪፎርሙን ውጤታማ በማድረግ የተጣለብንን ህዝባዊ ኃላፊነት ልንወጣ ይገባል ያሉት ደግሞ በወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ ዞን ፖሊስ በአዲስ የተመደቡ አመራሮች ተናግረዋል።

በመጨረሻም በአዲስ የተመደቡ አመራሮች በቅንነት እና በታማኝነት ህዝብን ለማገልገል ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top