በህገወጥ መልኩ የሚከናወኑ የተለያዩ የሎተሪ የዕጣ ተግባራት በወንጀል እንደሚያስጠይቁ ተገለፀ።

በህገወጥ መልኩ የሚከናወኑ የተለያዩ የሎተሪ የዕጣ ተግባራት በወንጀል እንደሚያስጠይቁ ተገለፀ።

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ ህገወጥ የሎተሪ ዕጣ ተግባራት ህገወጥነትን አስመልክቶ የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እና የክልሉ ፍትህ ቢሮ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የመኖሪያ ቤትን ጨምሮ የመኪና፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ልዩ ልዩ የእንሰሳት እና ለምግብ ፍጆታ የሚውሉትን በህገወጥ መንገድ የሎተሪ ዕጣ ማስወጣት ተግባራት በመበራከታቸው በመግለጫው ተገልጿል።

በዚህም የማታለል እና የማጭበርበር ወንጀሎች እየተከሰቱ እንደሚገኙ በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደጀን ወዳጅ ተናግረዋል።

እንደ ኮማንደር ደጀን ገለጻ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ዕድል ሎተሪ በሚል ህገወጥ ተግባር የተለያዩ የማታለል እና የማጭበርበር ወንጀሎች እየተፈፀሙ በማህበረሰቡ ላይ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እያስከተሉ ሲሆን ይህን ህገወጥ ተግባር ለመከላከልም የክልሉ ፖሊስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

አሰራሩ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር እውቅና ያልተሰጠው እንዲሁም የንግድ ፍቃድ የሌለው በመሆኑ በህግ ተጠያቂ ያደርጋል ያሉት ኮማንደር ደጀን በዚህ ህገወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላትም ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

አቶ ሙሉጌታ አሻግሬ በአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው ይህ ተግባር ያለ ንግድ ፈቃድ መተግበሩ ካለው ህገወጥነት ባሻገር ማህበረሰቡን ለማታለልና ለማጭበርበር ወንጀል እየዳረገ መሆኑ በመረጋገጡ በህግ የሚያስጠይቅ የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል።

በዚህ ህገወጥ የሎተሪ ዕጣ አሰራርም በርካታ ሰዎች እየተጭበረበሩ ላልተገባ የኢኮኖሚ ኪሳራ እየተዳረጉ መሆኑንም አንስተዋል።

በዚህ የወንጀል ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንዲሁም በዚህ አሰራር የተታለለም ይሁን ተግባሩ ሲፈፀም የተመለከተ ማንኛውም ህብረተሰብ ጉዳዩን ለሚመለከተው የህግ አካል መጠቆም ይኖርበታል ሲሉ አቶ ሙሉጌታ አክለው ተናግረዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top