የድጋፍ ሰልፉ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ ተጠናቋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለምረቃ መብቃቱን ተከትሎ በአማራ ክልል በሁሉም ዞኖች እና ወረዳዎች የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
የድጋፍ ሰልፉ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው ለሚገኙ የጸጥታ እና የደኅንነት አካላት ኦረንቴሽን ተሰጥቶ ወደ ስራ መገባቱን ነው ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) የገለጹት።
የአማራ ህዝብ ሰልፉ በሰላም እንዲካሄድ ከጸጥታ ኃይሉ ጎን በመሆን ላደረገው ቀና ትብብር ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ሲሉ ተናግረዋል።
ከሰልፉ ቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ሰልፉ በሰላም እንዲካሄድ እና ያለ አንዳች እንከን እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁ የመከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የጸጥታና ደኅንነት ግብረ-ኃይል እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ፣ ሚሊሻ እና ሰላም አስከባሪ አካላት ከፍ ያለ ምስጋና ይገባችኋል ሲሉ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) አክለው ተናግረዋል።









