የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም በመጠናቀቁ ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል።
ረዳት ኮሚሽነር አበበ ውቤ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል።
በክልላችን በደመቀ ሁኔታ የተከበረው የ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም ተከብሮ በመጠናቀቁ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምስጋና ያቀርባል ብለዋል።
ለዚህም የክልላችን ሰላም ወዳድ ህብረተሰብ ከፍተኛ ድርሻ መወጣቱን ምክትል ኮሚሽነሩ በመልዕክታቸው ተናግረዋል።።
በዓሉ በሰላም እንዲከበር አስተዋፅኦ ላበረከታችሁ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እንዲሁም ለፌደራል እና ለክልሉ የጸጥታ አካላት ላቅ ያለ ምስጋና ይገባችኋል ሲሉ ምክትል ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።
ከበዓሉ መዳረሻ ጀምሮ በዓሉ እስከ ተከበረበት ዕለት መላው የክልሉ ነዋሪዎች ከጸጥታ ኃይሉ ጎን በመሆን ከፍተኛ ሚና ስለተወጣችሁ በእኔና በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ሲሉ ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዡ ባስተላለፉት መልዕክት አብራርተዋል።

