መጭውን አዲስ ዓመት አስመልክቶ ከአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!!
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) መጭውን የአዲስ ዓመት አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ለመላው የክልላችንና የሀገራችን ማህበረሰብ እንኳን ለ2018 ዓ.ም አደረሳችሁ ያሉት ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) መጭው አዲስ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የመተሳሰብ ይሁንላችሁ ብለዋል።
የዘንድሮው አዲስ ዓመት ከወትሮው የተለየ የሚያደርገው የ14 ዓመታት የፅናትና የትግል ጉዞ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በተጠናቀቀበት ማግስት በመሆኑ ነው ሲሉ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።
አዲሱ ዓመት በፍቅር፣ በሰላም፣ በዕርቅና በመተሳሰብ የሀገራችንን ሉዐላዊነት በማስጠበቅ በጋራ የምንረባረብበት እና ወደ ማይቀረው የብልፅግና ጉዞ በከፍታ የምንነሳበት ዘመን እንዲሆን የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል ብለዋል።
በመቀጠል ለክልላችን ሰላም፣ ለህዝባችን ደህንነት የፌደራል የጸጥታ ተቋማት፣ የክልላችን ፖሊስ፣ አድማ ብተና፣ የፈጥኖ ደራሽ እንዲሁም ለሚሊሻ እና ሰላም አሰከባሪ አመራርና አባላት በያሉበት ሁሉ ለአዲሱ አመት እንኳን አደረሳችሁ በማለት ልባዊ ምኞቴን በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምረያ ስም እገልፃለሁ።

