በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላም እንዲኖር በትኩረት እየተሠራ ነው።

በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላም እንዲኖር በትኩረት እየተሠራ ነው።

በደብረ ብርሃ፣ በጎንደር፣ በኮምቦልቻ እና በደብረማርቆስ ከተማዎች የዞን የወንጀል መከላከል፣ የአድማ መከላከል ሻለቃ እና የሚሊሽ አመራሮች በጋራ ሲሰጥ የነበረውን የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቋል።

ስልጠናው ጠንካራ የጸጥታ ኀይል ለመፍጠር እና ክልሉ አስተማማኝ ሰላም የማስፈን ስራ እንዲያከናውን ለማስቻል እንዲሁም የክልሉን ሰላም ለማጽናት ዓላማ አድርጎ ስልጠናው መሰጠቱም ተጠቅሷል።

ክልሉ አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላም እንዲኖረው በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም በስልጠናው ላይ የተገኙ አመራሮች አስታውቀዋል።

የጸጥታ አካላት በአመለካከት፣ በአካል ብቃት እና በፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ብቁ እንዲሆኑ የተሰጠው ስልጠና ወሳኝ መሆኑም ተነስቷል።

ሕዝቡ የናፈቀውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ እና እየታዩ ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎችን ለማስቀጠል የጸጥታ ኀይሉ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

የጸጥታ አካላት የክልሉ ሕዝብ ከቦታ ቦታ በነጻነት እንዲቀሳቀስ ከማኅበረሰቡ ጋር በቅንጅት በመስራት ሰላምን ማጽናት እንዳለባቸውም ተጠቁሟል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት እና ክህሎት በመጠቀም የክልሉን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ስልጠናው ዕውቀት ያገኙበት እና ልምዳቸውን ያሳደጉበት መሆኑን የገለጹት ሰልጣኞች በቀጣይ ከሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀት እና ልምድ በመጠቀም ሰላምን ለማጽናት እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

ከማኅበረሰቡ ጋር በመሆን ሕግን ለማስከበር እያደረጉት ያለውን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አክለው ገልጸዋል።

የማኅበረሰቡ የልማት እንቅስቃሴ እና የምጣኔ ሀብት ተጠቃሚነት እንዲያድግ ሰላምን ለማጽናት ቁርጠኛ መሆናቸውንም የውይይቱ ተሳታፊዎች አንስተዋል።

ስልጠናው በክልሉ በአራት ማዕከሎች የተሰጠ መሆኑ ከአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top