የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እየተተገበረ በሚገኘው የክልሉ ፖሊስ ሪፎርም አፈጻጸም ሂደት ዙሪያ ውይይት እያካሄደ ነው።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እየተተገበረ በሚገኘው የክልሉ ፖሊስ ሪፎርም አፈጻጸም ሂደት ዙሪያ ውይይት እያካሄደ ነው።

በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ባለው ውይይት የተገኙት የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አበበ ውቤ የፖሊስን የመፈጸም ብቃት ለማሳደግ እንዲሁም ዘላቂ ሰላም ማስፈን የሚችል፣ በህዝብ ቅቡልነት ያለው፣ ገለልተኛ እና ህዝባዊ ተቋም ለመገንባት የሚያስችል የፖሊስ ሪፎርም ተግባራዊ እየተደረገ ነው ብለዋል።

ሪፎርሙ ተግባራዊ ከተደረገበት ጊዜ ወዲህ ራስን አብቅቶ ተልዕኮን በአግባቡ መወጣት የሚያስችሉ በርካታ ለውጦች ተመዝግበዋል ሲሉ ነው ምክትል ኮሚሽነሩ ያብራሩት።

በመድረኩ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሰው ኃብት አሰተዳደርና ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አብዮት ሽፈራው የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሪፎርም አፈጻጸም ሂደት ምልከታ የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል።

የክልሉ ፖሊስ ያካሄደው ሪፎርም ከግብ እንዲደርስ እና ተቋሙ ወደ ከፍታ እያደረገ ላለው ጉዞ በየደረጃው በሚገኝ አመራር እና አባላት በቁርጠኝነት ህዝብን ማገልገል ይጠበቅበታል ሲሉ ኮማንደር አብዮት ሽፈራው በጽሁፋቸው አመላክተዋል።

በተመሳሳይ በሸዋ ቀጠና ለሚገኙ የፖሊስ አመራሮች በደብረብርሃን ከተማ የክልሉ ፖሊስ እያከናወነ ያለውን የሪፎርም ስረዎች እና በስትራቴጅካዊ እቅዶች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ታደሠ አያሌው የክልሉ መንግስት የጸጥታ ኃይሉን ለማጠናከር እና ስብራቱን አቃንቶ የህዝብን ሰላም እና ደኅንነት ማስጠበቅ የሚችል፣ በሙያዊ ብቃቱ የተመሰከረለት ሰራዊት ለመገንባት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የክልሉ ፖሊስ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ተቋማዊ ጥናት በማካሔድ በጥናቱ ግኝት መሰረት የለውጥ ስራዎችን እየተገበረ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

ከፍተኛ አመራሩ በየደረጃው ላሉ አመራር እና አባላት የሪፎርሙን ሂደት በማስተዋወቅ አተገባበሩን መከታተል እና መደገፍ እንደሚገባ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ስትራቴጂክ አመራሮች አሳስበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top