ነባራዊ ሁኔታን የተረዳ እና ለሰላም መስፈን መስዋዕትነት የሚከፍል ቁርጠኛ መሪ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ።

ነባራዊ ሁኔታን የተረዳ እና ለሰላም መስፈን መስዋዕትነት የሚከፍል ቁርጠኛ መሪ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ።

የክልሉን ሰላም እና ደኅንነት በዘላቂነት መጠበቅ የሚያስችል የሰላም አስከባሪ እና የአድማ መከላከል ኃይልን ማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረገ ሥልጠና በደብረ ብርሃ፣ በጎንደር፣ በኮምቦልቻ እና በደብረማርቆስ ከተማዎች እየተካሄደ ነው።

ስልጠናው የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ የተገነዘበ እና ጠንካራ ወታደራዊ ተልዕኮን በብቃት መወጣት የሚችል የመሪ ብቃት ማሳደግ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

የኢትዮጵያን ብሎም የአማራ ክልልን ነባራዊ ሁኔታ የተረዳ እና ለሰላም መስፈን መስዋዕትነት የሚከፍል ቁርጠኛ መሪ መፍጠር ከመድረኩ የሚጠበቅ ውጤት መሆኑንም ተናግረዋል።

የሚመራውን ሠራዊት በብቃት እና በጠንካራ ወታደራዊ ዲሲፕሊን የሚመራ ሁለንተናዊ ብቃት ያለው የሰላም አስከባሪ ሠራዊት መገንባት ከመድረኩ የሚጠበቅ መሆኑ ተመላክቷል።

የክልሉ መንግሥት የሕዝቡን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ሥልጠናው እንተዘጋጀ የተገለጸ ሲሆን ስልጠናው በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እየተሰጠ መሆኑም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top