የVIP ጥበቃ ኮማንዶ ሰልጣኞች ተመርቀዋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የVIP ጥበቃ ኮማንዶ ሰልጣኞችን በብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማዕከል አሰልጥኖ አስመርቋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ እንዲሁም የዋና ጠቅላይ መምሪያው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር መላኩ ሲሳይ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ተገኝተዋል።
ፖሊስ የህዝብን አደራ ተሸክሞ ለሰላም ግንባታ ህይወቱን እስከ መስጠት ድረስ ዘብ የሚቆም ኃይል ነው ሲሉ ምክትል ኮሚሽነሩ እና የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተናግረዋል።
የVIP ጥበቃ ኮማንዶዎችን ማስመረቃችን የክልሉ ፖሊስ ወደ ከፍታ የመውጣት ምዕራፍ ማሳያ እና የሪፎርም ስራችን አካል ነው ብለዋል።
ስልጠናው ወታደራዊ ብቃትን በመላበስ ለሚያጋጥም ማንኛውም ሁኔታ አስፈላጊውን ምላሽ በመስጠት ተልዕኮን የመፈፀም ግብን ማሳካት የሚያስችል መሆኑንም ምክትል ኮሚሽነሩ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ለVIP ጥበቃ ኮማንዶ ሰልጣኞች የቴክኒክ፣ የአካል ብቃት እና የስነ-ምግባር ስልጠና መሰጠቱን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ በስልጠናው የሴቶች አቅም ጎልቶ የታየበት መሆኑንም አስታውቀዋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ሰላም እንዲሰፍን እና የህዝብ ደኅንነት እንዲረጋገጥ በሰው ኃይል ግንባታ ስራ አበረታች ውጤት እያመጣ እንደሚገኝ ምክትል ኮሚሽነር እና የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዡ አስገንዝበዋል፡፡
በመጨረሻም ይህ ስልጠና በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁኔታውን ላመቻቹ እና ለተባበሩ እንዲሁም ለብላቴ ልዩ ዘመቻዎች እዝ ማሰልጠኛ ማዕከል አመራር እና አባላት በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ስም ምክትል ኮሚሽነሩ ምስጋና አቅርበዋል።













