“እናንተ የሰላም አምባሳደር እና ጀግኖች ናችሁ” ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ(ዶ/ር)።

“እናንተ የሰላም አምባሳደር እና ጀግኖች ናችሁ” ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ(ዶ/ር)።

በክልሉ ከተለያዩ አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ ለመንግስት እጅ ለሰጡ የቀድሞ ታጣቂዎች በጎንደር ከተማ የተሐድሶ ስልጠና የማስጀመሪያ መርሃግብር እየተካሄደ ነው።

በማስጀመሪያ መርሀግብሩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) የፌዴራልም ሆኑ የክልላችን መንግስት ያደረጋቸውን የሰላም ጥሪዎች ተቀብላችሁ የመጣችሁ የቀድሞ ታጣቂዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።

ሰላም ይሻለናል ጦርነት አዋጪ አይደለም በማለት ለሰላም ቅድሚያ ሰጥታችሁ የመጣችሁ ሁሉ “የሰላም ጀግኖች ናችሁ” ሲሉም ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በፕሮግራሙ ላይም የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ፣ የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው፣ የአማራ ክልል ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አማረ ሰጤ፣ የርዕሰ መስተዳደሩ ልዩ አማካሪ አማኑኤል ፈረደ (ዶ/ር) እና የምዕራብ እዝ ምክትል አዛዥ ጄኔራል ዋኘው አለሜን ጨምሮ የዞን አመራሮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top