የህዝብን ሰላም በሚያውኩ አካላት ላይ የህግ ማስከበር ተጋድሏችን እንቀጥላለን ሲሉ የአድማ መከላከል ፖሊስ አባላት ተናገሩ።
የአማራ ክልል ህዝብን ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው የህግ ማስከበር ስራ መስዕዋትነት በመክፈል እና ግዳጃቸውን በብቃት ከሚወጡ የጸጥታ ኃይሎች መካከል የአማራ ክልል አድማ መከላከል ፖሊስ አንዱ ነው።
በደቡብ ጎንደር ዞን፣ በደብረታቦር ከተማና አካባቢው የሚገኙ የ3ኛ ሻለቃ የአድማ መከላከል ፖሊስ አባላት ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት የበጋው ሀሩር፣ የክረምቱ ዝናብና ቆፈን ሳይበግረን ተግባራችን የምንወጣው የህዝብን ሰላም የሚያውኩትን ለመከላከል እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ነው ብለዋል።
በደቡብ ጎንደር ዞን በተሰሩ በቅንጅታዊ የህግ ማስከበር ስራዎች ሰላም ማምጣት ተችሏል።
ህዝብን ሲያማርሩ የነበሩ የመኪና አስቁሞ ዘረፋና የግድያ ወንጀሎች በሚካሄድ ጥበቃ ወደ ሰላም መሻገር መቻሉም ተመላክቷል።
በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ታጣቂ ኃይሎች የሰላምን አማራጭ በመቀበል ወደ ማህበረሰቡ ተቀላቅለዋል ይህም የህግ ማስከበር ስራችን እና የማህበረሰቡ ተሳትፎ ያመጣው ውጤት ነው ሲሉ የአድማ መከላከል ፖሊስ አባላቱ አብራርተዋል።















