የመንግስትን የሠላም ጥሪ የተቀበሉ የታጠቁ ሀይሎች ወደ ተሀድሶ ስልጠና ማዕከል መግባታቸው ተገለጸ።

የመንግስትን የሠላም ጥሪ የተቀበሉ የታጠቁ ሀይሎች ወደ ተሀድሶ ስልጠና ማዕከል መግባታቸው ተገለጸ።

በሰሜን ሸዋ ዞን መርሐቤቴ ወረዳን ጨምሮ በበርካታ የዞኑ አካባቢዎች የታጣቁ ኃይሎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ስልጠና ማዕከል እየገቡ መሆኑን የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ንጉሴ ሞገስ አስታውቀዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ አለማየሁ ባለፍት ጊዜያት የተጀመረው በሰላም ታጣቂዎችን የመመለስ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።

ዋና አሥተዳዳሪው ከዚህ አንጻር ዞኑ ጥሩ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል።

የታጣቂዎች በሰላም መግባት በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ሚናው የጎላ እንደኾነም አንስተዋል።

ይህ ውጤት መንግሥት ለሰላም በሰጠው ትልቅ ዋጋ እና ሕዝቡ ለሰላም የሰጠው አወንታዊ ምላሸ እንደኾነ ነው ዋና አስተዳዳሪው የተናገሩት።

በሁሉም አካባቢዎችም ይህን ከመገዳደል የተሻለ ተሞክሮው ሊቀስሙ እንደሚገባም ገልጸዋል።

ዋና አሥተዳዳሪው በአንድ አካባቢ የሚወሰደው የሰላም እርምጃ ለሌላውም አካባቢ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው አሁን እየታየ ያለው በጎ እርምጃ እንዲሰፋም ጠንክረን እንሠራለን ብለዋል።

ለመጣው ውጤት መከላከያ ሠራዊት፣ የወረዳው መሪዎች እና የወረዳው ሕዝብ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

በተሃድሶ ስልጠና አቀባበል ፕሮግራም ላይ የሀገር መከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች፣ የፌደራል፣ የክልል እና የዞኑ የስራ ኃላፊዎች እና የጸጥታ አመራሮች መገኘታቸውን ኮማንደር ንጉሴ ሞገስ ተናግረዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top