የፖሊስ አመራሮችና አባላት ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ።
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የታች አርማጭሆ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አመራሮችና አባላት ህግን ከማስከበር ጎን ለጎን የበጎ አድራጎት ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ።
ለአብነትም ህዝብን ለማገልገል እና የህግ የበላይነት ለማስከበር ህይወታቸውን ላጡ ለፖሊስ እና ለሰላም አስከባሪ አባላት ልጆች የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
የፖሊስ አመራሮቹና አባላቶቹ ከትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ በተጨማሪም እርዳታ ለሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች የእህል ድጋፍ ማድረጋቸውን ከታች አርማጭሆ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታ።
ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችም ለተደረገላቸው ድጋፍ ለፖሊስ አባላቱ ልባዊ ምስጋና ማቅረባቸውንም ነው መረጃው የሚያመለክተው።





