የማህበረሰቡን ተሳትፎ በማጎልበት የቅድመ-ወንጀል መከላከል ስራን ማጠናከር እንሚገባ ተገለጸ።

የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ማህበረሰቡን ያሳተፈ የወንጀል መከላከል አሰራር ነው።

ተቀዛቅዞ የቆየውን የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል አሰራርን ዳግም እንዲያንሰራራ በማድረግ የሚከሰቱ ወንጀሎችን ለመከላከል ወደ ተግባር መግባቱን የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ግርማ እንኳሆነ የማህበረሰቡን ተሳትፎ በማጎልበት የቅድመ-ወንጀል መከላከል ስራን አጠናክረን እየቀጠልን እንገኛለን ብለዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት በክልሉ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ስራ መቀዛቀዙን ተናግረዋል።

አሁን ላይ ማህበረሰቡን ያተሳፈ የወንጀል መከላከል ተግባርን በማከናወን ዳግም እንዲያንሰራራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አዛዡ አንስተዋል።

የማህበረሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ የሚፈጠሩ የስርቆት፣ የእገታ፣ የግድያ እና መሰል ወንጀሎች መቀነሳቸውን ደግሞ ዋና ሳጅን መኮንን ለገሰ አብራርተዋል።

የሐይማኖት አባት እና የገብርዬ ክፍለ-ከተማ የሰላም ኮሚቴ አባል ቄስ ሙላቱ አግማስ ሰላም በሐይማኖታዊ ስርዓት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን ገልጸዋል።

ወንጀል በየትኛውም ሐይማኖት የተወገዘ በመሆኑ ከፖሊስ እና ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ስለ ሰላም በመምከር፣ በማስተማር ለጋራ ሰላም የጋራ ተሳትፎ እያደረግን እንገኛለን ሲሉ ቄስ ሙላቱ አክለው ተናግረዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top