“የምርመራ ስራችን ስናከናውን ህግን እና ሙያዊ ስነ-ምግባርን ተከትለን ሊሆን ይገባል” ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው

“የምርመራ ስራችን ስናከናውን ህግን እና ሙያዊ ስነ-ምግባርን ተከትለን ሊሆን ይገባል” ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው

በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው በአዲስ ለተመደቡ የወንጀል ምርመራ መምሪያ ኃላፊዎች እና ለዋና ክፍል ኃላፊዎች የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

“የምርመራ ስራችን ስናከናውን ህግን እና ሙያዊ ስነ-ምግባርን ተከትለን ሊሆን ይገባል” ሲሉ ምክትል ኮሚሽነሩ በሪፎርሙ ለተመደቡ አመራሮች በአጽንኦት ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እያካሄደ ያለው የሪፎርም ስራ በወንጀል ምርመራ ስራው ላይ ያበረከተው አዎንታዊ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ በዚህም ውጤታማ ተግባራትን ለመከወን መነሳሳትን የፈጠረ ነው ሲሉም አክለው ተናግረዋል።

የህዝብ አመኔታን ለመጎናፀፍ ከሙሰኝነት፣ ከጎጠኝነት እና ከብልሹ አሰራር የጸዳ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ነው ያሉት።

እንደ ምክትል ኮሚሽነሩ ገለጻ ማህበረሰቡ የሚፈልገውን ፍትህ እንዲያገኝ ቀን ከሌት በቁርጠኝነት በመስራት እውነተኛ የህዝብ አገልጋይ መሆናችንን በተግባር ማረጋገጥ ይገባናል።

የወንጀል ምርመራ ስራን ውጤታማ ለማድረግ ተናቦ እና ተረዳድቶ መስራት እንደሚያስፈልግም የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዡ አብራርተዋል።

የፎረንሲክ (የቴክኒክ ምርመራ) ባለሙያዎች ዘመኑን የዋጀ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን

በብቃት ተጠቅሞ ለፍትህን መረጋገጥ ሚናውን የሚወጣ መርማሪ ሆኖ መገኘት ይገባል ብለዋል።

ከፍትህ ተቋማት ጋር ያለንን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር የወንጀል ምርመራ አቅማችንን አጎልብተን ለፍትህ መረጋገጥ የበኩላችን ድርሻ ልንወጣ ይገባል ነው ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ።

በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታው ምክንያት ያልተቋጩ ስራዎች መኖራቸውን ያነሱት ምክትል ኮሚሽነሩ በዚህ በጀት ዓመት በሙሉ አቅማችን በመስራት እና የህዝቡን የፍትህ ጥያቄ በመመለስ ለፍትህ ስርዓቱ መጎልበት ተግተን እንስራ ሲሉ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዡ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top