በመኪና አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ

በመኪና አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላና ጠራ ወረዳ በቀን 18/12/2017 ዓ/ም በደረሰ የመኪና አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።

አደጋው የደረሰው 19 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ከደብረብርሀን ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ ሀይሩፍ በሚል የሚታወቀው አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ነው።

የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር በልኬ ይርጋ ፍጥነት ላይ የነበረው ተሽከርካሪ ጨኪ ቀበሌ ልቼ ጎጥ አካባቢ ጎማ ፈንድቶበት ሊገለበጥ ችሏል ብለዋል።

በዚህም የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 10 ተሳፋሪዎች ከባድ የአካል ጉዳት እንዲሁም ሰባት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት እንዳጋጠማቸው ገልጸዋል።

አሽከርካሪው ለጊዜው ከስፍራው መሰወሩን የተናገሩት ኮማንደር በልኬ የፍጥነት ወሰኑን አክብሮ በማሽከርክር በሰው እና በንብረት ላይ የሚደርሰውን ውድመት በጋራ እንከላከል ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በተመሳሳይ 18/12/2017 ዓ/ም በምዕራብ ጎጃም ዞን ጅጋ ንዑስ ወረዳ በተለምዶ ለዛ ወንዝ ከተባለው ስፍራ ከፍኖተ ሰላም ወደ አዲስ አበባ እየተጓዘ የነበረ ተሳቢ የጭነት መኪና ከባጃጅ ጋር ተጋጭቶ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የጅጋ ንዑስ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

በዚህም ከባጃጅ ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ 7 ሰዎች እና 2 እግረኞች በድምሩ የ9 ሰዎች ህይወት አልፏል።

አሽከርካሪው ለፖሊስ እጅ የሰጠ ሲሆን ፖሊስም የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ ያደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

ወቅቱ የክረምት በመሆኑ በጥንቃቄ እንዲሁም ሕግና ስርዓትን አክብሮ በማሽከርከር በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ የሚደርስን አደጋ መከላከል ይገባል! መልዕክታችን ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top