የከተማዋን ሠላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እያካሄደ ያለውን ሪፎርም ተከትሎ የደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ አዛዥ ሆነው የተመደቡት ኮማንደር ጥላሁን ታደሰ ከከተማዋ የጸጥታ አመራሮች ጋር ትውውቅ አካሂደዋል።
በትውውቅ መርሀ-ግብሩ ላይ የደሴ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ አዛዦች እና የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።
ኮማንደር ጥላሁን ታደሰ አመራሩ የተሰጠውን ኃላፊነት በቅንነትና በታማኝነት እንዲሁም በእኔነት ስሜት በመሰራት ደሴ ከተማ ሰላሟ የተጠበቀና ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን ማድረግ ተቀዳሚ ተግባራችን ሊሆን ይገባል ብለዋል።
የደሴ ከተማን ሰላምና ደኅንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከሰላም ወዳዱ የደሴ ከተማ ህዝብ ጋር በትብብር እንሰራለን ሲሉ ኮማንደር ጥላሁን አክለው ተናግረዋል::
ኮማንደር ጥላሁን ለከተማዋ ፖሊስ አመራሮች በቀጣይ ስለሚሰሩ የህግ ማስከበርና የጸጥታ ተግባሮች አቅጣጫ መስጠታቸውን የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።






