የትራፊክ አደጋዎችን ለመከላከል ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው።

የትራፊክ አደጋዎችን ለመከላከል ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው።

በክረምት ወቅት የሚፈጠሩ የትራፊክ አደጋዎችን ለመከላከል ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

በከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዋና ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር አዱኛው ምህረቴ የትራፊክ አደጋዎችን ለመከላከል ዕቅድ ተዘጋጅቶ እና ከባለሙያዎች ጋር ውይይት ተደርጎ ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል።

ለአሽከርካሪዎች፣ ለእግረኞች፣ ለበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች እና ለልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ህግን አክብሮ ስለመጓዝ እና ስለመንገድ አጠቃቀም የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መሰጠቱን ገልጸዋል።

እንደ ዋና ክፍል ኃላፊው ገለጻ የትራፊክ አደጋ ሊከሰትባቸው ይችላሉ የተባሉ የከተማዋ አካባቢዎች ላይ የትራፊክ ፖሊሶችን በመመደብ የተጠናከረ ቁጥጥር እየተደሰገ ይገኛል።

በበጀት ዓመቱ በትራፊክ አደጋ ምክንያት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር መሻሻል የታየበት ነው።

ለዚህም የትራፊክ ተቆጣጣሪ ፖሊሶች የማስተናበር እና የቁጥጥር ስራቸውን በተገቢው መንገድ መከወናቸው መሆኑን ኃላፊው አክለው ተናግረዋል።

በዓላት መድረሳቸውን ተከትሎ የሚፈጠሩ ወከባና መጨናነቆችን ለመቅረፍ እንዲሁም ተሳፋሪዎችን በማንገላታት እና በማዋከብ ለስርቆት እንዳይዳረጉ ከወንጀል መከላከል ክፍሎች እና ከትራንስፖርት ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ እነደሆነ ዋና ክፍል ኃላፊው አብራርተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top