“የአማራ ክልል ፖሊስ ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ውጤቶች መጠቀም የሚችል የሰው ኃይል ለመገንባት እየተሰራ ነው” ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር)

“የአማራ ክልል ፖሊስ ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ውጤቶች መጠቀም የሚችል የሰው ኃይል ለመገንባት እየተሰራ ነው” ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር)

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴን (ዶ/ር) እና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የተጀመረውን የስማርት ሲቲ ግንባታ ጎብኝተዋል።

ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) በጉብኝታቸው ዘመኑን የዋጁ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጠቀም የሚችል የሰው ኀይል ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በቴክኖሎጂ በመታገዝ የወንጀል መከላከል እና የወንጀል ምርመራ ስራዎችን ውጤታማ በማድረግ የፖሊስን አሰራር ቀልጣፋ እና ፍትሐዊ እንዲሆን ይሰራል ብለዋል።

በኮምቦልቻ ከተማ የተጀመረው የስማርት ሲቲ ግንባታ የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና የተለያዩ ውስብስብ ወንጀሎችን ለመከላከል ጉልህ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት።

የስማርት ሲቲ ግንባታው አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን እና መረጃን በቀላሉ ለመለዋወጥ የሚያስችል መሆኑን ኮሚሽነር ዘላለም(ዶ/ር) ተናግረዋል።

እንደ ኮሚሽነር ዘላለም(ዶ/ር) ገለጻ ዜጎች መረጃ የማግኘት መብታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማት ዝርጋታ ነው።

የስማርት ሲቲ ግንባታው የፖሊስን አገልግሎቶች ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ነው ሲሉ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) በጉብኝቱ ላይ ተገኝተው አብራርተዋል።

በመጨረሻም ለኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር እና ለኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዦች እና ምክትል አዛዦች ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) የምደባ ደብዳቤ እና የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top