“ሰላም በፖሊስ ጥረት ብቻ የማይመጣ እና የጋራ ርብርብን የሚሻ የወል ሀብታችን ነው” ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር)

በደሴ ከተማ ባለሀብቶች፣ በከተማዋ ነዋሪዎች እና በከተማ አስተዳደሩ ብርቱ ትብብር በደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ4ኛ ፖሊስ ጣቢያ የቢሮ ግንባታ ተጀምሯል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) በቦታው በመገኘት የግንባታ ሂደቱን ጎብኝተዋል።

ለዚህ ትውልድ ተሻጋሪ ሰናይ ተግባር ታሪክ የሰራችሁ የፖሊስ አመራር እና አባላት፣ አጋር የሰላም አርበኛ ባለሀብቶች እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ አመራሮች የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ላቅ ያለ ምስጋና አለው ብለዋል።

ሰላም በፖሊስ ጥረት ብቻ የማይመጣ እና የጋራ ርብርብን የሚሻ የወል ሀብታችን ነው ሲሉም ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የፖሊስ ጣቢያው ለከተማው ሰላም ትልቅ ዓቅም አለው ያሉት ኮሚሽነሩ ሰላማችንን ለማፅናት አንድ ርምጃ ከፍ ያልንበት ተግባር ነው ሲሉም አብራርተዋል።

የቢሮ ግንባታ ሂደቱን በቅርበት በመከታተል እና የግንባታ ቦታ አቅርቦቱን ላመቻቹት የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ምስጋና አቅርበዋል።

ወደ ፊትም ለፖሊስ ያላችሁን አጋርነት አጠናክራችሁ ልትቀጥሉ ይገባል ሲሉም ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) መልዕክት አስተላልፈዋል።

የፖሊስ ጣቢያው ከ4ሺህ 700 ካሬ ሜትር በላይ ስፋት ያለው እና ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት እንደተያዘለት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top