የፖሊስ አመራሮች እና አባላት አቅም ለሌላቸው ግለሰቦች ቤት ሰርተው አስረከቡ።

የፖሊስ አመራሮች እና አባላት አቅም ለሌላቸው ግለሰቦች ቤት ሰርተው አስረከቡ።

የአማራ ክልል ፖሊስ በማህበረሰባዊ እሴት ልክ የተመዘነ፣ በህዝብ አገልጋይነት ስሜት የተሸመነ ህዝባዊ ሰራዊት ነው።

የአማራ ክልል ፖሊስ ከመደበኛ ተግባራቸው ጎን ለጎን በልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ስራ ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ህዝባዊ ሰራዊትነታቸውን እያረጋገጡ ይገኛሉ።

ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስ የቀድሞው የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ እንደገለጹት በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ፖሊስ ከመደበኛ ተግባሩ ባለፈ በበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ የራሱን አበርክቶ እየተወጣ የህዝብ ወገንተኝነቱን እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል።

የጣቁሳ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት አመራሮች እና አባላት ከወር ደመወዛቸው ቀንሰው ከ87 ሺህ ብር በላይ በማሰባሰብ አቅም ለሌላቸው ግለሰቦች ቤት ሰርተው ማስረከባቸውን ኮማንደር አንተነህ ተናግረዋል።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ እና በምዕራብ ደንቢያ ወረዳዎች፣ በቆላ ድባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የፖሊስ አመራሮችና አባላትም ገንዘብ በማዋጣት የበጎ አድራጎት ስራዎችን መስራት መቻላቸውን ነው ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስ ለዝግጅት ክፍላችን የገለጹት።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top