ለVIP ጥበቃ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው።

ለVIP ጥበቃ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የህዝቡን ሰላምና ደኅንነት ለመጠበቅ ሰራዊቱን ተከታታይነት ባለው ስልጠና አቅሙን በማጎልበት የወንጀል መከላከል ብቃቱን በማሳደግ ላይ ይገኛል።

አሁን ላይ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተመለመሉ የVIP ጥበቃ ኮማንዶ ሰልጣኞች በብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል እየሰለጠኑ ይገኛሉ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሸነር አበበ ውቤ የስልጠና ሂደቱን ለመከታተል በስፍራው ተገኝተው የመስክ ጉብኝት አካሂደዋል።

እንደ ምክትል ኮሚሽነሩ ገለጻ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጣችሁን ስልጠና በሚገባ በመከታተል ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁ መሆን ይገባችኋል።

ስልጠና ብቻውን ግብ ስለማይሆን ወደ ተግባር ስትሰማሩ የሚጠበቅባችሁን ተቋማዊ አገልግሎት ለህብረተሰቡ መስጠት ይጠበቅባችኋል ብለዋል።

በጋራ እንደ አንድ አካል ሆናችሁ ስልጠናውን እንድትከታተሉ ሲሉም የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዡ ለሰልጣኝ ኮማንዶዎች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የዋና ጠቅላይ መምሪያው የሰው ኃብት አስተዳደርና ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አብዮት ሽፈራው በፖሊስ ሙያዊ ሰነ-ምግባር፣ የክልሉን ነባራዊ የጸጥታ ሁኔታ እንዲሁም የተቋሙን አሁናዊ የለውጥ ሂደት ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ሰጥተዋል።

ስልጠናው በቀጣይ በክልሉ የሚካሄዱ ታላላቅ ሁነቶች ላይ ከVIP ጥበቃ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በማስቀረት ተግባራቸውን በእውቀትና በክህሎት ለመስራት ያስችላል ሲሉ ኮማንደር አብዮት ገልጸዋል፡፡

በተግባር እና በንድፈ-ሀሳብ የሚሰጠውን ስልጠና በሚገባ እየተከታተሉ መሆኑን የተናገሩት ሰልጣኝ ኮማንዶዎች ከስልጠናው መጠናቀቅ በኋላ ተቋሙ በሚሰጠው የስራ ስምሪት የህዝብን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top