የአማራ ክልል ፖሊስ ስነ-ስርዓት ያከበረ የህዝብ አገልጋይነት ስሜት የተላበሰ ሰራዊት እንዲሆን እየተሰራ ነው።

የአማራ ክልል ፖሊስ ስነ-ስርዓት ያከበረ የህዝብ አገልጋይነት ስሜት የተላበሰ ሰራዊት እንዲሆን እየተሰራ ነው።

የአማራ ክልል ፖሊስ ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሏል።

የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በግንባር ቀደምትነት ከሚተገብራቸው የለውጥ (የሪፎርም ) ስራዎች መካከል የፖሊስን የቀደመ ተግባር እውን ማድረግ እና ፖሊሳዊ ስነ-ስርዓቶችን አክብሮ የሚያስከብር የፖሊስ ሰራዊት መገንባት ነው።

ይህንኑ ከሚያጎለብቱ ክዋኔዎች መካከል ፖሊሳዊ ስነ-ስርዓት የተከተለ የደምብ ልብስ አሟልቶ መልበስ፣ ንፅህናን መጠበቅ፣ ሰዓት ማክበር እና በወታደራዊ የሰልፍ ስነ-ስርዓት ባንዲራን ማውጣትና ማውረድ ናቸው።

በክልሉ ሁሉም የፖሊስ ጣቢያዎች እና ጽሕፈት ቤቶች በየሳምንቱ ሰኞ ጠዋት ከመደበኛ ተግባራት በፊት ሁሉም የፖሊስ አባላትና አመራሮች የሚያደርጉት የፎሌን ቁጥጥር (የወታደራዊ ሰልፍ ስነ-ስርዓት) ያከናውናሉ።

ይህ ተግባር የአማራ ክልል ፖሊስ ስነ-ስርዓት ያከበረ የህዝብ አገልጋይነት ስሜት የተላበሰ ሰራዊት እንዲሆን ከሚያደርጋቸው ጥረቶች መካከል አንዱ ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top