የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየምን ጎበኙ።
ሙዚየሙን የጎበኙት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየውን የአመራር ስልጠና ያጠናቀቁ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ስትራቴጅክ እና ከፍተኛ አመራሮች ናቸው።
የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ በጉብኝታቸው ባዩት ነገር መደሰታቸውን በመግለጽ ሀገራችን ለሳይንስ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቷን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ቴክኖሎጅን በመጠቀም ጥራት ያለው፣ ፍትሐዊ የሆነ እንዲሁም ቀልጣፋ አገልግሎት ለህዝቡ ለመስጠት እንድንችል ያነሳሳን ጉብኝት ነው ሲሉ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ አብራርተዋል።









