“ፖሊስ ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን የልማቱ አንድ አካል በመሆን የራሱን ሀገራዊ አሻራ ማስቀመጥ ይኖርበታል” ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር)

“ፖሊስ ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን የልማቱ አንድ አካል በመሆን የራሱን ሀገራዊ አሻራ ማስቀመጥ ይኖርበታል” ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር)

“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር የ7 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ የአማራ ክልል እና የፌደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በባህርዳር ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሂደዋል።

የችግኝ ተከለ መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዶክተር ዘላለም መንግስቴ ልማትና ሰላም የማህበረሰባችን ፍላጎት በመሆኑ የፖሊስ ሰራዊቱ ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን የልማቱ አንድ አካል በመሆን የራሱን ሀገራዊ አሻራ ማስቀመጥ ይኖርበታል ብለዋል።

በሀገራዊ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ ሰራዊቱ መሳተፉ የራሱን አሻራ በማስቀመጥ የሰላም እና የልማት አርበኛ የሆነ ሰራዊት ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል ኮሚሽነር ዶክተር ዘላለም መንግስቴ።

በሰራዊታችን ውስጥ ችግኝ መትከል ትልቅ ትርጉም ያለው የልማት ተግባር በመሆኑ ሀገራዊ አሻራችን አስቀምጠናል ያሉት ደግሞ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነርና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አበበ ውቤ ናቸው።

የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብና እንዲጸድቁ በማድረግ ሰራዊታችን ከህዝብ ጎን ሆኖ የልማት አጋርነቱን የሚያረጋግጥበት ተግባር መሆን ይገባል ሲሉ ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

በችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ ላይ ከክልሉ የፀጥታ አካላት በተጨማሪም የፌደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት ተገኝተው ሀገራዊ አሻራቸውን አስቀምጠዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top