ፖሊስ ሰላምና ደኅንነት ከማስከበር ጎን ለጎን ሀገራችን በምታካሄዳቸው የልማት ስራዎች ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ።
በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ስልጠና እየወሰዱ ያሉ የአማራ ክልል ፖሊስ ስትራቴጅክና ከፍተኛ አመራሮች በዛሬው ዕለት በሰንዳፋ በኬ ከተማ እና በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ የችግኝ ተከላ አካሄደዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ፖሊስ ሰላምና ደኅንነት ከማስከበር ጎን ለጎን ሀገራችን በምታካሄዳቸው የልማት ስራዎች ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረገ ነው ብለዋል።
ፖሊስ ወንጀል መከላከል ተግባሩ ባሻገር በሀገር የልማት ስራዎች መሳተፍ አለበት ሲሉ በችግኝ ተከላው የተሳተፉ የአማራ ክልል ፖሊስ አመራሮች ተናግረዋል።






