የፌዴራል ፖሊስ እያከናወነ ያለውን በቴክኖሎጂ የታገዘ የወንጀል መከላከል ስራ ጎብኝተዋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ስትራቴጂክ እና ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እየወሰዱ ካሉት የአመራር ስልጠና ጎን ለጎን በፌደራል ፖሊስ ዋና መሳሪያ ቤት ተገኝተው እየተከናወነ ያለውን በቴክኖሎጂ የታገዘ የወንጀል መከላከል ተግባራትን እንዲሁም የሎጂስቲክ አጠቃቀም እና አጠቃላይ የሪፎርም ስራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የተሳተፉ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ የፌዴራል ፖሊስ እያከናወነ ያለው ሁሉን አቀፍ የለውጥ ስራዎች ልምድ የምንወሰድበት ነው ብለዋል።
የአማራን ህዝብ ሰላም እና ደኅንነት ለመጠበቅ በቴክኖሎጂ የታገዘ የወንጀልን መከላከል ስራን እና ሌሎች ፖሊሳዊ ተግባራትን በመከወን የህዝብ ከገልጋይነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ ተናግረዋል።








